ቀጥታ፡

ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በተለያዩ ዘርፎች ትብብራቸውን ለማጠናከር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፤መጋቢት 26/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በተለያዩ ዘርፎች ትብብራቸውን ለማጠናከር ስምምነት ተፈራረሙ።

4ኛው የኢትዮ-ኡጋንዳ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

በስብሰባውም ሁለቱ ሀገራት ግንኙነታቸውን በተለያዩ ዘርፎች ለማጠናከር ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።


 

ስምምነቶቹ ኢትዮጵያንና ኡጋንዳ በንግድ፣ግብርና፣አቪየሽን፣ ትምህርት፣ኢነርጂ፣ ጤናና በሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ግንኙነት ወደ ላቀ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግሩ ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፣ የኢትዮጵያ እና የኡጋንዳ ትብብር ዘመናትን የተሻገረ መሆኑን ገልጸዋል።

የሁለቱ ሀገራት ትብብር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

የዛሬው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባና የተፈረሙ የትብብር ስምምነቶች የሀገራቱን ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል።


 

የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦዶንጎ ጄጄ አቡበክር በበኩላቸው፤ የኡጋንዳ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በህዝብ ለህዝብ የተሳሰረ ነው ብለዋል።

ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም