የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተጨባጭ ውጤት ያስመዘገቡ ኢንዱስትሪዎችን እየጎበኙ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተጨባጭ ውጤት ያስመዘገቡ ኢንዱስትሪዎችን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2017(ኢዜአ)፡- የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተሞች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተጨባጭ ውጤት ያስመዘገቡ ኢንዱስትሪዎችን በመጎብኘት ላይ ናቸው።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ማሳደጉ ይታወቃል።
ንቅናቄው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በጥራትና በብዛት ለማምረት እንዲሁም የግብርና እና ማዕድን ምርቶች ላይ ዕሴት ጨምሮ ለገበያ ለማቅረብ አዲስ ምዕራፍ መክፈቱም እንዲሁ።
የሀገራዊ ንቅናቄው ዋና ዋና ዓላማዎች የአምራች ኢንዱስትሪውን ችግሮች በጋራ በመፍታት ለዘርፉ ዘላቂ ልማትና ተወዳዳሪነት ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ዘርፉ ለኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲወጣ ማስቻል ነው።
እንዲሁም በዘርፉ ያለውን የሥራ ባህል ማሻሻል ብሎም የኢንዱስትሪ ምርቶችን ጥራትና ተወዳዳሪነት በማሻሻል ገቢ ምርቶችን የመተካት ሽፋንን ማሳደግ ናቸው፡፡
የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተሞች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተጨባጭ ውጤት ያስመዘገቡ ኢንዱስትሪዎችን ዛሬ በመጎብኘት ላይ ናቸው።
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አበባ ታመነ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የጉብኝቱ አላማ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ወደ ስራ የተመለሱ ኢንዱስትሪዎችን የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል።
በንቅናቄው በተፈጠሩ ቅንጅታዊ አሰራሮች የዘርፉን ማነቆዎች በመለየት ተዘግተው የነበሩ ኢንዱስትሪዎች ወደ ምርት መመለሳቸውን ጠቁመዋል።
በጉብኝቱ በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተሞች ከዚህ ቀደም ተዘግተው የቆዩ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተጨባጭ ውጤት ያስመዘገቡ ኢንዱስትሪዎች የጉብኝት አካል ናቸው።