ሦስተኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2017(ኢዜአ)፡- ሦስተኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ፎረሙ እየተካሄደ የሚገኘው "ሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊነት በኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

በፎረሙ ላይ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና ምክትል አፈ ጉባዔ ሎሚ በዶ፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ዘሃራ ዑመድ፣ በህዘብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ(ዶ/ር)፣ የምክር ቤቱ አባላት፣ ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በፎረሙ የኢትዮጵያ እና የዓለም ሕገ መንግሥቶች የታሪክ ጉዞ ላይ ያተኮሩ ፅሁፎች እየቀረቡ እንደሚገኝ የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል።

የሕገ-መንግሥት ሪፎርም፤ የሕገ-መንግሥቱ ቅቡልነትና ተግዳሮት ሀገራዊ መግባባት በኢትዮጵያ የሚዳስሱ ገለፃዎችም በምሁራን እየቀረቡ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም