ቀጥታ፡

ባለስልጣኑ እና ምክር ቤቱ በጋራ መስራት መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2017(ኢዜአ)፦ የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አቅም ግንባታን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች በትብብር መስራት  የሚያስችላቸውን ስምምነት ዛሬ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ አህመድ ሁሴን ናቸው።


 

ስምምነቱን አስመልክቶ የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የትብብር ማዕቀፉ በሁለቱ ወገኖች መካከል የትብብርና እና ምክክርን፣ የአቅም ግንባታ እና የመረጃ ልውውጥን ማጠናከር፣ ሀገር አቀፍ የመረጃ ማዕከልን ማደራጀት እና የጋራ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ተግባራዊ ማድረግን እንደሚያካትት ገልጸዋል።

ስምምነቱ በሀገር ልማት ላይ ያላቸውን የጋራ ትብብር የበለጠ እንደሚያጠናክርም አመልክተዋል።


 

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ አህመድ ሁሴን በበኩላቸው ስምምነቱ የማህበረሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችንም የሚደግፍና የሚያጋጥሙ ችግሮች ለመፍታት እንደሚያስችል ተናግረዋል።

በስምምነቱ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የምክር ቤቱ የስራ አስፈጻሚዎች መገኘታቸውን የባለስልጣኑ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም