የአድዋ ድል መታሰቢያ የዛሬውን ትውልድ ስነ አዕምሯዊ የሀገር ፍቅርና ወኔ የሚገነባ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአድዋ ድል መታሰቢያ የዛሬውን ትውልድ ስነ አዕምሯዊ የሀገር ፍቅርና ወኔ የሚገነባ ነው
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2017(ኢዜአ)፦ የአድዋ ድል መታሰቢያ የዛሬውን ትውልድ ስነ-አዕምሯዊ የሀገር ፍቅርና ወኔ የሚገነባ መሆኑን የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ስታፍ ሰራተኞች ገለጹ።
የዩኒቨርሲቲ ስታፍ ሰራተኞቹ የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።
ሰራተኞቹ የድል መታሰቢያው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ነፃነት ለውጭ ወራሪ ኃይል ሳያስደፍሩ ዘላለም ለትውልድ በኩራት ያሻገሩ ጀግኖችን ታሪክ አጉልቶ የሚያሳይ ነው ብለዋል።
የአሁኑን ትውልድ ስነ አዕምሯዊ የሀገር ፍቅር ወኔና ጀግንነት የሚቀሰቅስ እንደሆነ መግለጻቸውንም ከሀገር መከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።