የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ከሃዋሳ ከተማ ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ከሃዋሳ ከተማ ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፤መጋቢት 25/ 2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ዛሬም ቀጥሎ ሲውል ሶስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
በዚህም ከምሽቱ 12 ሰዓት የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ከሃዋሳ ከተማ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ኢትዮጵያ መድን በ41 የአንደኝነቱን ደረጃ ይዟል። ሃዋሳ ከተማ በ20 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
መድን ጨዋታውን ካሸነፈ ከተከታዩ ባህር ዳር ከተማ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 11 ከፍ ያደርጋል።
በአንጻሩ ለሃዋሳ ከተማ ማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና እንዲወጣ ያደርገዋል።
በሌሎች መርሃ ግብሮች ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከ30 ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከፋሲል ከነማ፣ ወላይታ ድቻ ከመቀሌ 70 እንደርታ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በተያያዘም ትናንት በተደረጉ የ23ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ድሬደዋ ከተማ አዳማ ከተማን 3 ለ 1 ሲረታ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀድያ ሆሳዕና ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።