ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ መርሃ ግብር የሚካሄድበት ቀን እና ቦታ ይፋ ሆኗል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ሚያዚያ 18 እና 19 ቀን 2017 ዓ.ም በሃዋሳ ከተማ እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

በዚሁ መሰረት ሸገር ከተማ ከወላይታ ድቻ ሚያዚያ 18 ፣ ሲዳማ ቡና ከመቻል ሚያዚያ 19 ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም