ቀጥታ፡

ለውጡ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የመነሳት ዘመን ነው - ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2017(ኢዜአ)፡- ለውጡ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የመነሳት ዘመን መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የመጋቢት 24 ሀገራዊ ለውጥን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤልን ጨምሮ፣ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራሎች እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።


 

ቀኑን አስመልክቶ "የመጋቢታውያን የለውጥ ፍሬዎች የነገ ተስፋዎች ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና" በሚል ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ ነው።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት፤ ለውጡ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የመነሳት ዘመን ነው ብለዋል።

ባለፉት የለውጥ አመታት በፌደራል ፖሊስ በርካታ ስኬታማ የሆኑ የሪፎርሞች ተግባራዊ መከናወናቸውን ገልፀዋል።

በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂ ማዘመን፣ በአደረጃጀት፣ በአሰራር፣ የወደፊት እይታን ተረድቶ በመስራት ስኬታማ የሪፎርም ሥራ ተሰርቷል ብለዋል።

ይህም የፖሊስን የማድረግ አቅምን በወንጀል መከላከልም ሆነ የወንጀል ምርመራ ሥራዎችን በመስራት እንዲያድግ ማስቻሉን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም