ቀጥታ፡

የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በቁርጠኝነት ይሰራል - ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ገለጹ።

በቅርቡ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የተመደቡት ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በፖሊስ ኮሚሽኑ የማኔጅመንት አባላት እና መኮንኖች የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።


 

ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በወቅቱ እንዳሉት ፖሊሳዊ ብቃት እና ስብዕናን የተላበሰ የተሰጠውን ተልዕኮ የሚወጣ ዘመናዊ ፖሊስና አደረጃጀት ግንባታ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

በክልሉ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በጋራ እና በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።


 

የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሰው ኃብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ በበኩላቸው በከፍተኛ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ለህብረተሰቡ ሰላም በጋራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም