የዓለም አቀፉ የጅምናስቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የዓለም አቀፉ የጅምናስቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2017 (ኢዜአ)፦ የዓለም አቀፉ የጅምናስቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሞሪናሬ ዋታናቤ የኢትዮጵያን የጅምናስቲክ ስፖርት እንቅስቃሴ ለመጎብኘት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ገበያው ታከለ እና የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የዓለም አቀፍ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሞሪናሬ ዋታናቤ በቆይታቸው የኢትዮጵያ ጅምናስቲክ ስፖርት ያለበትን ደረጃ የተመለከተ ግምገማ እንደሚያደርጉ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ፕሬዝዳንቱ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን እንደሚጎበኙ እና ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር እንደሚወያዩም ተገልጿል።