ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምትከተለው አካሄድ ተገቢ ነው - የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምትከተለው አካሄድ ተገቢ ነው - የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤መጋቢት 22/2017(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የጀመረችው ሰላማዊ የዲፕሎማሲ አካሄድ ተገቢ መሆኑን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ።
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የባሕር በርን ለመጠቀም ያቀረበችው ጥያቄ ሰላማዊና የዲፕሎማሲ አካሄድ ተገቢነት አለው።
ኢትዮጵያም የባሕር በርን ለመጠቀም ያቀረበችው ጥያቄ አስፈላጊና መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ጠቁመዋል።
ለኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የሚኖርባት እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማስቀጠል የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምትከተለው ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን የባህር በር መሻት ለፍትሕ ቀናዒ የሆኑ የዓለም አገሮች ሁሉ በትክክል ያዩታል የሚል እምነት አለኝ ያሉት አምባሳደር አብርሃም፤ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የተሸከመች ሀገር የባህር በር አጥታ ልትኖር አይገባትም ብለዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄም እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚ ለማስተናገድ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህን ሁኔታ የማይረዳ መንግስትም ሆነ አገር ስለማይኖር በሰላማዊ የዲፕሎማሲ አካሄድ መፍትሔ የሚያገኝ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።
የባህር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና የህዝቦቿን ተጠቃሚነት ለማስቀጠል መፍትሔ ማግኘት እንደሚገባው አስገንዝበዋል።