ቀጥታ፡

የአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ በባህርዳር ከተማ ይካሄዳል - ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ በባህርዳር ከተማ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው የአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ከመጪው ቅዳሜ መጋቢት 27/2017 ዓ.ም ጀምሮ በባህርዳር ከተማ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም