ወላይታ ድቻ ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል - ኢዜአ አማርኛ
ወላይታ ድቻ ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 21/2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋኔጫ የመጨረሻ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ሃዋሳ ከተማን በመለያ ምት በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል።
በሃዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ በተደረገው ጨዋታ ካርሎስ ዳምጠው በ35ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ወላይታ ድቻ መሪ ሆኖ ነበር።
ከእረፍት መልስ በ56ኛው ደቂቃ ሃዋሳ ከተማ ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ታፈሰ ሰለሞን ወደ ግብ በመቀየር ቡድኑን አቻ አድርጓል።
ጨዋታው በመደበኛ 90 ደቂቃ በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ አሸናፊውን ለመለየት ወደ መለያ ምት አምርቷል።
በዚህም ወላይታ ድቻ 3 ለ 2 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል።
ወላይታ ድቻ አምና የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ተፋላሚ ነበር።
በሌላ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ መቻል ኢትዮጵያ መድንን 3 ለ 1 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
ሸገር ከተማ እና ሲዳማ ቡና ትናንት ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ ማለፋቸው ይታወቃል።