1446ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም ተከብሮ ተጠናቋል - የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ - ኢዜአ አማርኛ
1446ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም ተከብሮ ተጠናቋል - የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 21/2017(ኢዜአ)፡- በመላው ሀገሪቱ የተከበረው 1446ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከተው ለመላው የሀገራችን ሕዝብ እና ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በተለይም ለሀይማኖት አባቶች፣ ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎችና ለወጣቶች ምስጋና አቅርቧል።
ፌደራል ፖሊስ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ከበዓሉ ዋዜማ ጀምረው የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ ለተወጡ የፀጥታ ኃይሎች የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ያመሰግናል ብሏል።