ቀጥታ፡

1ሺህ 446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በጂንካ፣ በሆሳእና፣ በአርባ ምንጭ፣ በሚዛን አማን ፣ በዲላ፣ በቦንጋና በአሶሳ ከተሞች እየተከበረ ነው

ጂንካ/ሚዛን አማን/አርባ ምንጭ/ ቦንጋ/ ዲላ/ አሶሳ፤ መጋቢት 21/2017(ኢዜአ)፡- 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በጂንካ፣ በሚዛን አማን፣ በአርባ ምንጭ፣ በዲላ፣ በቦንጋና በአሶሳ ከተሞች በኢድ ሶላትና በሌሎች ሀይማኖታዊ ስነ-ስርአቶች እየተከበረ ነው፡፡

በአሉ በጂንካ በቀድሞ አየር ማረፊያ፣ በአርባምንጭ በጃሚ መስጂድ አደባባይ፣ በሆሳዕና በአብዮ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በተለይም በሆሳዕና ከተማ በአብዮ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም እየተከበረ ባለው በአል ላይ የሀድያ ዞን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ ኢማም ግርማ ሙዘይን ጨምሮ የሀይማኖቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።

በአሉ ዲላ፣ በሚዛን አማን፣ በወልቂጤ፣ ሆሳዕናና አሶሳ ከተሞችም በስግደትና በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም