ቀጥታ፡

ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲያከብር በቂ ዝግጅት ተደርጓል - የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በመላው ሀገራችን ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲያከብር በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው ኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በመላው ሀገራችን ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲያከብር በቂ ዝግጅት አድርጎ ወደ ተግባር በመግባት ተልዕኮውን በተገቢው እየተወጣ ይገኛል ብሏል፡፡

መላው የሀገራችን ሕዝብ ለበዓሉ መከበር እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ለማስወገድ በሚካሄደው የፀጥታ ማስከበር ሥራ ላይ በባለቤትነት በመሳተፍ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ የበለጠ አጠናክሮ በመቀጠል፤ የፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት በዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ(EFP App) እና በ991 ነፃ የስልክ መስመር እንዲሁም በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን እያቀረበ በድጋሚ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆን ተመኝቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም