ኢድ አልፈጥር በዓልን የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ማሳለፍ ይገባል - የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ - ኢዜአ አማርኛ
ኢድ አልፈጥር በዓልን የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ማሳለፍ ይገባል - የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2017(ኢዜአ)፦ ኢድ አልፈጥር በዓልን የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና በመደጋገፍ ማሳለፍ እንደሚገባ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለጸ።
1 ሺ 446ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል አስመልክቶ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
ጉባኤው ለኢዜአ በላከው መግለጫ፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወር ሃይማኖታዊ ስርዓቱ በሚያዘው መሰረት የተቸገሩ ወገኖቻችን በመርዳት፣ የታመሙትን በመጠየቅና በመንከባከብ በፆምና በዱዓ ማሳለፉን ገልጿል።
በረመዳን ወር የታየው ሃይማኖታዊ የመረዳዳት፣ መተባበር፣ የትህትና፣ የፍቅር እና የአንድነት በጎ ተግባር በሌሎች ወራትም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ኢድ አልፈጥር በዓልን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና በማገዝ ሊሆን እንደሚገባ በመግለጫው ተገልጿል።