ሚኒስትሩ የብሔራዊ ሁለገብ የወተት ልማት ስልጠና ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ - ኢዜአ አማርኛ
ሚኒስትሩ የብሔራዊ ሁለገብ የወተት ልማት ስልጠና ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2017(ኢዜአ)፦ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኦሮሚያ ክልል ሆለታ ከተማ የብሔራዊ ሁለገብ የወተት ልማት ስልጠና ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠዋል፡፡
ማዕከሉ በአምስት ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ባለሶስት ወለል ሕንፃ ሲሆን ለግንባታው 200 ሚሊዬን ብር ወጪ ይደረግበታል ተብሏል፡፡
ሚኒስትር በወቅቱ እንዳሉት የሚገነባው ማዕከል ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት በወተት ልማት ዘርፍ የሚያጋጥመውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ችግር መፍታት ያስችላል።
በወተት ምርትና ምርታማነት እሴት ሰንሰለት ውስጥ የቴክኒክ ባለሙያዎቹን እውቀትና ክህሎት መጠቀም የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይሄውም በአገር አቀፍ የወተት ምርትና ምርታማነት ላይ አወንታዊ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአርብቶ እና ከፊል አርብቶ አደሮችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድግ እና የሥራ እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የስልጠና ማዕከሉ አዳቃይ ከቴክኒክ ባለሙያዎች በተጨማሪ በእንስሳት እርባታ ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸው፤ ግንባታው በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ሥራ እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ የማዕከሉን የመሰረት ድንጋይ ካስቀመጡ በኋላ የሆለታ እንስሳት ልማት ማዕከልን አጠቃላይ