ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ የፓርላሜንታዊ ትብብራቸውን ለማጠናከር እንደሚሹ ገለጹ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2017 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ የፓርላሜንታዊ ትብብራቸውን የበለጠ የማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ።

በናይጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለገሰ ገረመው በናይጄሪያ የታችኛው ምክር ቤት የኢትዮ-ናይጄሪያ የወዳጅነት ቡድን ሊቀመንበር ሰንደይ ሲሪያከስ ኡሜሃ የተመራ ልዑካን ቡድን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ መካከል ስላለው ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት አስመልክቶ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።

የፓርላሜንታዊ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጎልበት እና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንደሚሰሩ አንስተዋል።

ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በአፍሪካ ጉዳዮች እና የጋራ ፍላጎታቸው በሆኑ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉም በአቡጃ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም