ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሃ ግብር

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ።

ባህር ዳር ከተማ ከሸገር ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት፣ ሲዳማ ቡና ከሀዲያ ሆሳዕና ከቀኑ 9 ሰዓት በሃዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ይጫወታሉ።

መርሃ ግብሩ ነገም ቀጥሎ ሲውል መቻል ከኢትዮጵያ መድን እና ሃዋሳ ከተማ ከወላይታ ድቻ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ክለብ ኢትዮጵያ ወክሎ በቀጣዩ ዓመት በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ በ1937 ዓ.ም የተጀመረ አንጋፋ የጥሎ ማለፍ ውድድር ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም