ቀጥታ፡

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች መጋቢት 24 ምክንያት በማድረግ የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤መጋቢት 20/2017(ኢዜአ)፡-መጋቢት 24 የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን የመጣበት እና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሰረት የተጣለበት እለትን ምክንያት በማድረግ ነው ውድድሩ እየተደረገ ያለው።

በሩጫው ውድድር ላይ በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ አመራሮች፤አባ ገዳዎች እና ሀዳ ሲንቄዎችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተገኝተዋል።


 

የኢዜአ ሪፖርተሮችም በክልሉ ሸገር ከተማ አስተዳደር፤በአዳማ ከተማ፤ጀማን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ሁነቱን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም