ቀጥታ፡

አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም ከአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ የአፍሪካ ፖሊሲ ከፍተኛ ፕሮፌሽናል ስታፍ አባል ጆን ቶማስዜውስኪ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤መጋቢት 19/2017 (ኢዜአ)፦በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም ከአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ የአፍሪካ ፖሊሲ ከፍተኛ ፕሮፌሽናል ስታፍ አባል ጆን ቶማስዜውስኪ ጋር  በዋሺንግተን ዲሲ ተወያይተዋል።

አምባሳደር ብናልፍ ከቶማስዜውስኪ ጋር ግልጽ እና ጠቃሚ ውይይት ማድረጋቸውን በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

በውይይቱ ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ያለውን አሁናዊ የግንኙነት ሁኔታ ገምግመዋል።

የሁለቱ አገራት ግንኙነቱ ይበልጥ ሊጠናከር በሚችልባቸው መንገዶች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

በቅርበት ተገናኝቶ የመስራትን ጠቀሜታን በውይይታቸው አጽንኦት የሰጡት ጉዳይ ሲሆን በቀጣይ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን አጠናክሮ ለመቀጠል መስማማታቸውን ኤምባሲው በመረጃው አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም