ቀጥታ፡

ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ለፊቼ ጫምባላላ የዘመን መለወጫ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2017 (ኢዜአ)፦የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ለሲዳማ ብሔር የዘመን መለዋጫ ፊቼ ጫምባላላ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በመልዕክታቸው ፊቼ ጫምባላላ የአብሮነት ፣የአንድነትና የሰላም ተምሳሌት የህዝቦችን የእርስ በርስ መስተጋብር የሚያጠናክር የሲዳማ ብሔር ድንቅ እሴት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በዓሉ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ መሆኑ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን  ዓለም አቀፍ መልክ እንዲኖረው ማድረጉን አመልክተዋል።

በዓሉ የሰላም እና ጤና እንዲሆን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም