ቀጥታ፡

ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ለፊቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2017(ኢዜአ)፦ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ለሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጫምባላላ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል::

የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ የሆነው ፊቼ ጫምባላላ የሰላም የእርቅና ሌሎች እሴቶች ጎልተው የሚታዩበት የሲዳማ አባቶች ባማረና ባሸበረቀ ባህልና ስርዓት የሚያከናውኑት ብሩህ ተስፋ የሚሰነቅበት የዘመን መለወጫ በዓል ነው።

በዓሉ የባህል መገለጫ የአንድነት የህብር የፍቅርና የሰላም እሴቶች ይበልጥ የሚያጎላ እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።

በድጋሚ እንኳን ለፊቼ ጫምባላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውንገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም