ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

እንኳን ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ - ፍቼ ጫምባላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ኢትዮጵያ በብዝሃ ማንነት፣ ባህልና እሴቶች የደመቀች፣ በህብረ ብሔራዊነት የተጋመደች ታላቅ ሀገር ናት፡፡

የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ የሆነው ፍቼ ጫምባላላ በዓል በረጅም የትውልድ ሰንሰለት ውስጥ እዚህ የደረሰ ድንቅ በዓል ነው፡፡ በዓሉ የሲዳማ ብሔር ባህላዊ መታወቂያ ቅርስ ከመሆን አልፎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሀብት ጭምር ነው፡፡

የፍቼ ጫምባላላ በዓል ለሲዳማ ህዝብ ልዩ ቦታ አለው፡፡ የተጣላው የሚታረቅበት፤ ሩቅ ያለው አብሮ ከቤተሰብ ጋር ለመሆን የሚሰበሰብበት፤ ወደ ነገ በአዲስ ራዕይ፤ በአዲሰ ተስፋ የመሸጋገሪያ በዓል ነው።

በድጋሜ እንኳን ለፍቼ ጫምባላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

አይዴ ጫምባላላ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም