አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2017(ኢዜአ)፡- በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ቤንጃሚን ቦል ሜል (ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገዋል።
አምባሳደር ነቢል ውይይቱ በደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ እና ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።