በማዕከሉ የሚሰለጥኑ ሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማላቅ አስፈላጊውን ድጋፍ ይደረጋል - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል - ኢዜአ አማርኛ
በማዕከሉ የሚሰለጥኑ ሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማላቅ አስፈላጊውን ድጋፍ ይደረጋል - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2017(ኢዜአ)፡- በማዕከሉ የሚሰለጥኑ ሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማላቅ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል ሲሉ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።
ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከ"ለነገዋ" የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በማዕከሉ የሚሰለጥኑ ሴቶችን ተጠቃሚነት ማላቅ ላይ ባተኮረው የውይይት መድረክ የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሂርጳሳ ጫላ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤልሻዳይ ክፍሌ ተገኝተዋል፡፡
ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በውይይቱ እንደገለጹት፤ በማዕከሉ የሚሰለጥኑ ሴቶች በሥራ ገበያው ላይ ተፈላጊ የሆነ ክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማላቅ ይሰራል፡፡
በክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ መስኩ ያሉ ዕድሎችን እንዲጠቀሙ ከማድረግ ባሻገር የማዕከሉ አቅም ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲያድግ ሚኒስቴሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡