የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓለም አቀፍ የቅድመ ክፍያ ማስተር ካርድ ይፋ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓለም አቀፍ የቅድመ ክፍያ ማስተር ካርድ ይፋ አደረገ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓለም አቀፍ የፕላስቲክ እና ቨርቹዋል የቅድመ ክፍያ ማስተር ካርድን ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዓለም አቀፉ የክፍያ ተቋም ማስተር ካርድ ጋር በመተባበር የማስተር ካርድ ቅድመ ክፍያ ሥርዓትን አስጀምሯል።
በይፋ ማድርጊያ ስነ-ስርአቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ፣ የማስተር ካርድ የአፍሪካ ፕሬዚዳንት ማርክ ኤሊዮትን ጨምሮ የንግድ ባንክ እና የማስተር ካርድ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ በወቅቱ እንደገለጹት ባንኩ የዲጂታል ቴክኖሎጂን በማሳደግ አገልግሎቱን እያዘመነ ይገኛል።
የቅድመ ክፍያ ማስተር ካርዱ የባንኩን ዲጂታል አገልግሎት ይበልጥ እንደሚያዘምነው አስታውቀዋል።
የማስተር ካርድ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ማርክ ኤሊዮት በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያስጀመረው ዲጂታል አገልግሎት አለም አቀፍ አገልግሎቱን ይበልጥ የሚያቀላጥፍ መሆኑን አንስተዋል።
በቀጣይ ማስተር ካርድ ከባንኩ ጋር ዲጂታል ቴክኖሎጂን የማሳደግ ስራ ላይ በጋራ እንደሚሰራም ተናግረዋል።