ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደርን ተቀብለው አነጋገሩ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2017(ኢዜአ)፡- የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቭርሃም ንጉሤን(ዶ/ር) በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ውይይታቸው የኢትዮጵያን እና የእስራኤልን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።


 

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቭርሃም ንጉሤ(ዶ/ር) ከፕሬዝዳንት ታዬ ጋር የነበራቸውን ውይይት በተመለከተ ለኢዜአ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በውይይታችን የኢትዮጵያ እና እስራኤል ግንኙነት ልዩ፣ ጥልቅ እና ታሪካዊ መሆኑን አንስተናል ብለዋል።

ሁለቱ ሀገራት በኢኮኖሚ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በደን ልማት፣ በቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በሞደርናይዜሽን እና በጤና ዘርፎች በትብብር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም