በሐረሪ ክልል በለውጡ ዓመታት ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል

ሐረር፤ መጋቢት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል በለውጡ ዓመታት ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት መመዝገቡን  የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጉዳዮች  ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሃላፊ አቶ ተውፊቅ መሀመድ  በክልሉ ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት ሰላምና ጸጥታን ከማረጋገጥ አንጻር የተከናወኑ ስራዎችና የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ ተውፊቅ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት በክልሉ ባለፉት ሰባት  የለውጥ ዓመታት ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በተከናወነው ስራ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ።

"በዘርፉ ህዝቡን በማሳተፍ የተከናወነው ስራ ጉልህ ሚና አበርክቷል " ብለዋል።

በክልሉ መንግሥትም መልካም አስተዳደር የማስፈንና የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራ በትኩረት መከናወኑን አመልክተዋል።

በክልሉ አስተማማኝ ሰላም በመረጋገጡ በህዝብና በመንግስት ትብብር በከተማና በገጠር  በርካታ የልማት ስራዎች  መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በህዝቦች መካከል አብሮነት የጎለበተበት፣ እህትማማችነትና ወንድማማችነት የዳበረበት መሆኑን ጠቅሰዋል ።

የተገኘው ውጤት የለውጡ ትሩፋት መሆኑን የጠቀሱት አቶ ተውፊቅ በተለይ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የአባ ገዳዎች አስተዋጾ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም