የሶማሌ እና የአፋር ክልሎች ህዝቦች የሰላም እና የልማት ፎረም ተመሰረተ - ኢዜአ አማርኛ
የሶማሌ እና የአፋር ክልሎች ህዝቦች የሰላም እና የልማት ፎረም ተመሰረተ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2017(ኢዜአ)፡- የሶማሌ እና የአፋር ክልሎች ህዝቦች የሰላም እና የልማት ፎረም ተመሰረተ።
የሶማሌ እና የአፋር ክልሎች ህዝቦች የወንድማማችነት ግንኙነት ማጠናከሪያ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታዎች ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) እና ቸሩጌታ ገነነ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።
በዚሁ መድረክ የሶማሌ እና የአፋር ክልሎች ህዝቦች የሰላም እና የልማት ፎረም ተመስርቷል።
የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት ፎረሙ የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች ለጋራ ሰላም እና አንድነት የሚሰሩበት ነው።
እንዲሁም በጋራ እሴቶቻቸው እና የወንድማማችነት ግንኙነትን ለማጠናከር የሚመክሩበት መሆኑን ገልጸዋል።