ኪርጊስታን በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ልትከፍት ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኪርጊስታን በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ልትከፍት ነው

አዲስ አበባ፤መጋቢት 17/2017 (ኢዜአ)፦ኪርጊስታን በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ልትከፍት መሆኑ ተገለጸ።
ተቀማጭነታቸውን በፓኪስታን በማድረግ በኪርጊስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር በፓኪስታን የኪርጊስታን አምባሳደር አቫዝቤክ አታክሃኖቭ ጋር ተወያይተዋል።
ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው የጋራ ፍላጎታቸው በሆኑ ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን የሁለትዮሽ፣ቀጣናዊ እና የባለብዝሃ ወገን ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
በውይይቱ ላይ ኪርጊስታን በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ለመክፈት መወሰኗ ተገልጿል።
አምባሳደር ጀማል የኪርጊስታን ኤምባሲ መከፈት የሁለቱን ሀገራት የፖለቲካ፣ኢኮኖሚ እና ባህል ትብብር ይበልጥ እንደሚያጎለብት ገልጸዋል።
በፓኪስታን የኪርጊስታን አምባሳደር አቫዝቤክ አታክሃኖቭ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ እንደሆነች ተናግረዋል።
መረጃው በኢስላማባድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው።