ቀጥታ፡

የኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በትኩረት መስራት ይገባል-ቋሚ ኮሚቴው

አዲስ አበባ፤መጋቢት 17/2017 (ኢዜአ)፦የኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳስቧል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በአማራ ክልል በደሴና ኮምቦልቻ የሚገኙ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን የስራ እንቅስቃሴ ምልከታ እያደረገ ይገኛል።

የኮሚቴው አባላት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮምቦልቻ አየር ማረፊያን የአገልግሎት አሰጣጥ እና የማስፋፊያ ግንባታ ሂደትን ጎብኝቷል።

የቡድኑ መሪ ዘውዱ ታደሰ (ዶ/ር) አየር መንገዱ ባለው ውስን ቦታ ሳይገደብ በርካታ ቁጥር ላላቸው ደንበኞች እየሰጠ ያለውን አገልግሎት በጥንካሬ አንስተዋል።

የማስፋፊያው ግንባታ ሂደቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ አሳስበዋል። ቋሚ ኮሚቴው የግንባታውን ሂደት አስመልክቶ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል ብለዋል።

በአየር ማረፊያው የሚሰጡ አገልግሎቶች የህብረተሰቡን ፍላጎት ባሟላ መልኩ ማጠናከር እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው ማሳሰቡን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም