አምባሳደር ገነት ተሾመ ከሩሲያ ስትራቴጂካዊ ጥናቶች ኢኒስቲትዩት ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ገነት ተሾመ ከሩሲያ ስትራቴጂካዊ ጥናቶች ኢኒስቲትዩት ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤መጋቢት 17/2017 (ኢዜአ)፦በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ(ዶ/ር) ከሩሲያ ስትራቴጂካዊ ጥናቶች ኢኒስቲትዩት ዳይሬክተር እና ከሩሲያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካይል ፍራድኮቭ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ እንዲሁም በሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር።
ተቋማዊ ትስስርን መፍጠር እና በሀገራቱ የምርምር ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሀሳብ መለዋወጣቸውን አምባሳደር ገነት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በባለሙያዎች ደረጃ ቋሚ የምክክር መድረክ በመፍጠር የዓለም አቀፍ ግንኙነት ስርዓት መቀየር ላይ በጋራ እንደሚሰሩም አመልክተዋል።