የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ከስዊድን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር እና የወጪ ንግድ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ከስዊድን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር እና የወጪ ንግድ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2017(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከስዊድን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር እና የወጪ ንግድ ሚኒስትር ዲያና ጃንስ ጋር ዛሬ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ ያተኮረው አፍሪካ ህብረት እና ስዊድን በሁለትዮሽ እና የባለብዝሃ ወገን ማዕቀፎች ያላቸውን አጋርነት ማጠናከር በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ መሆኑን ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ስዊድን ለኮሚሽኑ እና ለህብረቱ አባል ሀገራት እያደረገች ያለውን ድጋፍ እና ለጋራ የልማት ፍላጎቶች ያላትን አበርክቶ አድንቀዋል።