ቀጥታ፡

በአማራ ክልል በሪፎርም አተገባበር ላይ የሚመክር የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

ባህርዳር ፤ መጋቢት 16/2017(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አተገባበር ላይ የሚመክር የንቅናቄ መድረክ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩን ያዘጋጀው የአማራ ክልል ስቪል ሰርሺስና የሰው ሀብት ልማት ኮሚሽን ሲሆን ንቅናቄውም በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አተገባበር ላይ ይመክራል ተብሏል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሸነር መኩሪያ ሃይሌ(ዶ/ር)፣ የክልሉ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይዘሮ ባንችአምላክ ገብረማርያምን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የከተማ አሰተዳደር አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

ሲቪል ሰርቪሱ ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት በሚል መሪ ሀሳብ እየተከናወነ ያለው የንቅናቄ መድረክ ነፃና ገለልተኛ ስቪል ሰርቪስ በመገንባት ቀልጣፋና ዘመናዊ  አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ እርካታን ለማረጋገጥ የሚያግዝ መሆኑ ተመላክቷል።

መድረኩም የመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርምና በአንድ ማዕከል አገልግሎት አተገባበር ዙሪያ በሚቀርቡ ሰነዶች ላይ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያሰቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም