በቻይና ናንጂንግ የተሳተፈው ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አቀባበል ተደረገለት

አዲስ አበባ፣መጋቢት 16 /2017 ( ኢዜአ)፦) በቻይና ናንጂንግ በተካሄደው 20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑክ ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የጀግና አቀባበል ተደርጓል።

ለልዑኩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ መኪዩ መሀመድ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች አቀባበል አድርጎላቸዋል።

ኢትዮጵያ በሻምፒዮና ከዓለም 3ኛ እንዲሁም ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን ማጠናቀቋ ይታወቃል። መረጃው የኢትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም