የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ታላቁን የረመዳን ፆም በማስመልከት የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሄደ

አዲስ አበባ፤መጋቢት 15/2017 (ኢዜአ)፦የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻልኢንስቲትዩት ታላቁን የረመዳን ፆም አስመልክቶ የጋራ የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሄደ። 

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ሙስሊሙ ማህበረሰብ  በፆም እና ሌሎች እምነቱ በሚያዛቸው የአምልኮ ተግባራት በሚተጉበት በታላቁ  የረመዳን ወቅት አብሮትን የሚያጠናክርበት ስራዎችን በመስራት ወንድማማችነትን ማጠናከር ተገቢ ነው ብለዋል። 

በታላቁ የረመዳን ወር  ደግነትን ለሌሎች ማዳረስን፣ ይቅር መባባልን ማስፈን፣ ትዕግስትን መለማመድ፣ የተቸገሩትን ማገዝ እና  መሰል ሰብአዊ እሴቶች የሚያጠናክርበት ወር ነው ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም አብሮነትን የሚያጠናክሩ ስራዎችን በመስራት በጋራ ለሀገራችን ብልፅግና እና ሰላም መትጋት ይገባናል ብለዋል። 

የኢፍጣር መርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች ዝግጅቱ በሰራተኞች መካከል መቀራረብንና መተሳሰብን በመፍጠር ወንድማማችነትን እንደሚያጠናክር መናገራቸውን ከኢንስቲትዩቱ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም