ኢትዮጵያ ጅቡቲን በሰፊ የግብ ልዩነት በማሸነፍ በማጣሪያው የመጀመሪያ ድሏን አስመዝግባለች

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2017 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ስድስተኛ የምድብ ጨዋታ ጅቡቲን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፋለች።

ማምሻውን በሞሮኮ ኤል ጀዲዳ ከተማ በሚገኘው ኤል አብዲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቡበከር ናስር በጨዋታ ሁለት፣  በፍጹም ቅጣት አንድ ጎል በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል።

በተመሳሳይ በረከት ደስታ ሁለት በጨዋታ፣ አንድ በፍጹም ቅጣት በማግባት ሀትሪክ መስራት ችሏል።

ሳሙኤል አኪንቢኑ ለጅቡቲ ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከተሎ በምድብ አንድ የምትገኘው ኢትዮጵያ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው የመጀመሪያ ድሏን አስመዝግባለች።

በምድቡ በስድስት ነጥብ ደረጃዋን ከ5ኛ ወደ 4ኛ አሻሽላለች።

በማጣሪያው አምስተኛ ሽንፈቷን ያስተናገደችው ጅቡቲ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን 6ኛ ደረጃን ይዛለች።

በተያያዘም በዚሁ ምድብ ዛሬ በተደረገው ጨዋታ ቡርኪናፋሶ ከሜዳዋ ውጪ 2 ለ 1 አሸንፋለች።

ውጤቱን ተከትሎ ቡርኪናፋሶ ነጥቧን ወደ 11 ከፍ በማድረግ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ምድቡን በ13 ነጥብ የምትመራው ግብጽ ነገ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በካይሮ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሴራሊዮንን ታስተናግዳለች።

ሴራሊዮን በ8 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም