የኢትዮጵያ እና ብራዚል የቢዝነስና ኢንቨስትመንት ፎረም በሳኦፖሎ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ እና ብራዚል የቢዝነስና ኢንቨስትመንት ፎረም በሳኦፖሎ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እና ብራዚል የቢዝነስና ኢንቨስትመንት ፎረም መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም በብራዚል ሳኦፖሎ ከተማ ይካሄዳል።
ፎረሙ የኢትዮጵያን እምቅ የኢንቨስትመንት፣ የንግድ እና ቱሪዝም አቅም ማስተዋወቅ ያለመ መሆኑን በብራዚል የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
ሁነቱ የኢትዮጵያ እና ብራዚልን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር የማጠናከር ፋይዳ እንዳለውም ተገልጿል።
የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅም የሚያስተዋውቅ ፎረም በየካቲት ወር 2017 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በተገኙበት በብራዚሊያ መካሄዱ የሚታወስ ነው።