ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት የስራ ላይ የቡድን ስብሰባ ብሔራዊ ጥቅሟን በሚያስጠብቅ መንገድ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት የስራ ላይ የቡድን ስብሰባ ብሔራዊ ጥቅሟን በሚያስጠብቅ መንገድ እየተከናወነ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ ለዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት የተደረገውን አምስተኛ ዙር ድርድር በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ከ23 ዓመታት በላይ ድርድር ስታደርግ መቆየቷን አስታውሰዋል።

ኢትዮጵያ በታዛቢነት በቆየችበት የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን አምስተኛ ዙር ቡድን ስብሰባ ላይ መድረሷን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን በተደረገው ስብሰባ ከ20 በላይ ድጋፍ ያገኘችበት ከፍተኛ አሀዝ መሆኑን ገልጸዋል።

የዓለም የንግድ ድርጅት የዓለምን 95 በመቶ ህዝብ የያዙ 166 ሀገራትን ያቀፈ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለአባልነት ጥያቄ ካቀረቡ 22 ሀገራት ኢትዮጵያ የተሻለ የድርድር ሂደት ላይ መሆኗን ተናግረዋል።

ስድስተኛው ዙር ድርድር በመጪው ሐምሌ ወር እንደሚካሄድም ሚኒስትሩ አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም