ቀጥታ፡

በለውጡ ዓመታት ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጠናከር ገዥና አሰባሳቢ ትርክቶችን በመገንባት ረገድ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል

ሐረር፤መጋቢት 15/2017 (ኢዜአ)፥በለውጡ ዓመታት ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጠናከር ገዥና አሰባሳቢ ትርክቶችን በመገንባት ረገድ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን በብልጽግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በልማት፣በዴሞክራሲ ግንባታ ሂደትና ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ረገድ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በተመለከተ በብልጽግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፥ በለውጡ ሰባት ዓመታት በተለይም ሀገራዊ አንድነትን ከማፅናት አንፃር ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጠናከር ገዥና አሰባሳቢ ትርክቶችን በመገንባት ረገድ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ዘርዝረዋል።

በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርአት እየዳበረ እንዲሄድ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት፤ በኢትዮጵያ አግላይ የነበረውን የፖለቲካ ተሳትፎ በማስቀረት ህብረ ብሄራዊነት የሚስተዋልበት እውነተኛ የዴሞክራሲ ስርአት መዘርጋት መቻሉንም አንስተዋል።

በሀገሪቱ በስፋት ይስተዋሉ የነበሩ ዋልታ ረገጥ እሳቤዎችና ነጠላ ትርክቶችን በመተው ወደ አሰባሳቢና ገዥ ትርክቶች ለመሸጋገር የሚያስችሉና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ተግባራት በስፋት ተከናውነዋል ብለዋል።

በመሆኑም በለውጡ ዓመታት ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጠናከር ገዥና አሰባሳቢ ትርክቶችን በመገንባት ረገድ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ነው የጠቀሱት።

መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በይፋ የተበሰረው የለውጡ መንግስት በርካታ ውስብስብ ፈተናዎችን ወደ ድል እየቀየረ በሁሉም ዘርፎች አኩሪና ዕምርታዊ ውጤቶች እያስመዘገበ ቀጥሏል ብለዋል።

በመሆኑም የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በማጠናከር ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲመዘገብ በማድረግ የኢትዮጵያን ብልፅግና የማረጋገጥ ጥረት በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።

“የመጋቢት 24 ፍሬዎችና ቀጣይ የሀገራችን ተስፋዎች” በሚል መሪ ሀሳብ በሀረሪ ክልል የለውጡን ሂደት በተግባር የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በቀጣይነት የሚከናወኑ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም