የአልጄሪያ የኢነርጂ፣ማዕድንና የታዳሽ ሐይል ሚኒስትር መሀመድ አርካብ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የአልጄሪያ የኢነርጂ፣ማዕድንና የታዳሽ ሐይል ሚኒስትር መሀመድ አርካብ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤መጋቢት 15/2017(ኢዜአ):-በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የአልጄሪያ የኢነርጂ፣ማዕድንና የታዳሽ ሐይል ሚኒስትር መሀመድ አርካብ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ሁለቱ አገራት በኢነርጂ፣ማዕድን እና ታዳሽ ኃይል ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ሊያጠናክር የሚችል ውይይት ከተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚያደርጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።