ስፔን፣ ፈረንሳይ፣ ፖርቹጋል እና ጀርመን ለግማሽ ፍጻሜ አለፉ 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2017 (ኢዜአ)፦ በዩኤፋ ኔሽንስ ሊግ ኤ ሻምፒዮንሺፕ የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ማምሻውን ተደርገዋል።

በዚህም ስፔን ኔዘርላንድን፣ ፈረንሳይ ክሮሺያን፣ ጀርመን ጣልያንን እና ፖርቹጋል ዴንማርክን በደርሶ መልስ ወጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።

በዚህም ፈረንሳይ ከስፔን እና ፖርቹጋል ከጀርመን እ.አ.አ ጁን ወር 2025 የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።


እ.አ.አ በ2018 የተጀመረው ዬኤፋ ኔሽንስ ሊግ የአውሮፓ ሀገራት የሊግ ውድድር ፎርማት ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም