የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ርክክብ እና ዓለም አቀፍ የውሃ ቀን አከባበር መርሃ ግብር በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ርክክብ እና ዓለም አቀፍ የውሃ ቀን አከባበር መርሃ ግብር በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው
አርባምንጭ፤ መጋቢት 13/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ርክክብ እና ዓለም አቀፍ የውሃ ቀን አከባበር መርሃ ግብር በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው መርሃ ግብር ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ "የኢትዮጵያ የውሃ ዲፕሎማሲ ባለፉት 3 ክፍለ ዘመናት" በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።
እንዲሁም የታላቁ ህዳሴ ግድብ በናይል ተፋሰስ ሀገራት ስለሚኖረው ፋይዳ ላይ ያተኮረ ጽሑፍ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አባይ ወርቁ በኩል ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግም ተገልጿል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ ዋንጫ ርክክብ እንደሚደረግም ተመልክቷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራር አባላት፣ ምሁራን፣ የጋሞ ሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ታዳሚዎችም ተገኝተዋል።