ቀጥታ፡

10ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና መምህራን የስፖርት ሊግ ውድድር ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2017(ኢዜአ)፡- 10ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና መምህራን የስፖርት ሊግ ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም መካሄድ ይጀምራል።

ውድድሩ "የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድርን ባህል በማድረግ ጤናማ፣ ንቁ እና ብቁ ትውልድ እንፈጥራለን" በሚል መሪ ሀሳብ ነው የሚካሄደው።


 

ውድድሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በጋራ እንዳዘጋጁት ከከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም