ዋልያዎቹ ድል አልቀናቸውም - ኢዜአ አማርኛ
ዋልያዎቹ ድል አልቀናቸውም
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2017 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ23ኛ የፊፋ ዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ማጣሪያ በግብፅ 2 ለ 0 ተሸንፏል።
እኩለ ሌሊት ላይ በሞሮኮ ካዛብላንካ በሚገኘው ላርቢ ዛውሊ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሐመድ ሳላህ እና ዚዞ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ አንድ በሶስት ነጥብ 5ኛ ደረጃን ይዛለች።
ግብጽ ምድቡን በ13 ነጥብ እየመራች ነው።
ዋልያዎቹ በማጣሪያው ስድስተኛ የምድብ ጨዋታቸውን ሰኞ መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጅቡቲ ጋር ያደርጋሉ።
በተያያዘም በምድብ አንድ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ቡርኪናፋሶ ጅቡቲን 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፋለች። ቡድኑ በ8 ነጥብ 2ኛ ደረጃን ይዟል።
ቡርኪናፋሶ ቀጣይ የምድብ ጨዋታዋን የፊታችን ሰኞ ከጊኒ ቢሳው ጋር ታደርጋለች።