ሰላም በኢትዮጵያ ልብ ውስጥ በደማቁ የታተመ የዘመናት መሻት ነው - ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ - ኢዜአ አማርኛ
ሰላም በኢትዮጵያ ልብ ውስጥ በደማቁ የታተመ የዘመናት መሻት ነው - ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ የሰላም መሻት በልቧ በደማቁ የታተመ የዘመናት ጽኑ ፍላጎቷ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ።
ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ኢትዮጵያ ሰላምን አጥብቃ እንደምትሻ እና ለለውጥ ጉዞዋ ወሳኝ መሆኑን በውል ትገነዘባለች ብለዋል በኤክስ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ወደ ጦርነት ትገባለች የሚለውን መሰረተ ቢስ ስጋት እንዲሁም ግጭት እና ውድመት ይከሰታል ቀቢጸ ተስፋ ያላቸውን አካላት የማይጨበጥ ምኞት እንደማይሳካ በንግግራቸው እንዳረጋገጡ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ፍላጎት ሰላም እና ልማት ብቻ እንደሆነም በግልጽ ያሰመሩበት ጉዳይ ነው ብለዋል።