የጅቡቲ ትራንዚተርስ ማህበር ለኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ እውቅና አበረከተ - ኢዜአ አማርኛ
የጅቡቲ ትራንዚተርስ ማህበር ለኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ እውቅና አበረከተ
አዲስ አበባ፤መጋቢት 11/2017(ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በሎጅስቲክስ ዘርፍ ላሳየው አጋርነት ከጅቡቲ ትራንዚተርስ ማህበር እውቅናና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) ጅቡቲ በመገኘት ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡
የጅቡቲ ትራንዚተርስ ማህበር የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ በሎጀስቲክስ ዘርፍ በአብሮነት ላበረከተው ጉልህ አስተዋጽኦና ቀልጣፋ አገልግሎት የሰጠው እውቅና መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) ሽልማቱን በተቀበሉበት ወቅት እንዳሉት፤ ሽልማቱ የሁለቱን ሀገራት አብሮነት የሚያሳይና ወንድማማችነት የሚየጎለብት ነው፡፡
ከዚህም ባለፈ በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ጤናማ የሎጂስቲክስ ዘርፍ እንቅስቃሴን ለማጎልበት የላቀ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
በዘርፉ የጭነት ምጣኔ ከፍታን በመጨመርና ገቢን በማሳደግ፣ ግንኙነቶችን በማጠናከር፣ሥራ እድል በመፍጠር ጠንካራ ኢኮኖሚን ማረጋገጥና የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡