ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህልን በተመለከተ ከተናገሯቸው ጉዳዮች መካከል

በኢትዮጵያ ሁለት መሰረታዊ ስብራቶች አሉ፤ አንደኛው የመጠፋፋት ባህል ነው። መንግስታት ወደ ኃላፊነት ሲመጡ ሳይደራጁ ለማጥፋት የሚደረግ ሙከራ ማለት ነው። ይህ በበርካታ የኢትዮጵያ መንግስታት ታሪክ ተሞክሯል።

ሁለተኛው ከሶሻሊስት እሳቤ ጋር በስፋት ወደ ኢትዮጵያ የገባው በሽታ ነው። ይህ በኢትዮጵያ ያመጣው ችግር ፍረጃ ነው። የጠላትና የወዳጅ ፍረጃ ማለት ነው። ይህም ለሰላማዊ ድርድር ቦታ አይሰጥም። ይህም በኃይል ስልጣን የመያዝ አባዜን አምጥቷል።ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስተዋለ ያለውም ችግር ይህ ነው። በምርጫ የተመረጠን መንግስት በኃይል ለመጣል የሚሞክሩ ኃይሎች አሉ። የሚገርመው ነገር ግን የሚያሰቃዩት እንታገልልሃለን የሚሉትን ህዝብ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም